Skip to content
የBible App ዓርማ

ማቴዎስ 19:1 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ማቴዎስ 19:1 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ኢየሱስ ይህን ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ፣ ገሊላን ትቶ ከዮርዳኖስ ማዶ ወዳለው ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደ።

ማቴዎስ 19:1 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ኢየሱስ ይህን ተናግሮ ካበቃ በኋላ ከገሊላ ተነሥቶ፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወደምትገኝ ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ።

ማቴዎስ 19:1 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ኢየሱስም ይህን ነገር ከፈጸመ በኋላ፥ ከገሊላ ሄዶ ወደ ይሁዳ አውራጃ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ መጣ።

ማቴዎስ 19:1 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ኢየሱስም ይህን ነገር ከፈጸመ በኋላ፥ ከገሊላ ሄዶ ወደ ይሁዳ አውራጃ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ መጣ።

ማቴዎስ 19:1 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ፥ ከገሊላ ወጥቶ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ወደ ይሁዳ አውራጃ መጣ።