ማቴዎስ 13:54 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ማቴዎስ 13:54 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ወደ ገዛ አገሩ መጣ፤ በምኵራባቸውም ሕዝቡን ያስተምር ጀመር። እነርሱም በመገረም እንዲህ አሉ፤ “ይህ ሰው ይህን ጥበብና እነዚህን ታምራት የማድረግ ኀይል ከየት አገኘ?
ያጋሩ
ማቴዎስ 13 NASVማቴዎስ 13:54 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ወደ አገሩ ወደ ናዝሬት ከተማ መጥቶ በምኲራቦቻቸው ሕዝብን ያስተምር ነበር፤ የሰሙትም ሁሉ በመደነቅ እንዲህ ይሉ ነበር፤ “ይህ ሰው ይህን ጥበብና ይህን ድንቅ ሥራ ከወዴት አመጣው?
ያጋሩ
ማቴዎስ 13 አማ05ማቴዎስ 13:54 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር፤ እንዲህም አሉ “ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?
ማቴዎስ 13:54 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር፤ እንዲህም አሉ፦ ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?
ያጋሩ
ማቴዎስ 13 አማ54ማቴዎስ 13:54 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ በምኵራባቸው ያስተምራቸው ነበር፥ ተገርመውም እንዲህም አሉ “ይህን ጥበብና ኃይል ከየት አገኘው?