ማቴዎስ 12:18 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ማቴዎስ 12:18 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“እነሆ፤ የመረጥሁት፣ የምወድደውና ነፍሴ ደስ የተሠኘችበት ብላቴናዬ፣ መንፈሴን በርሱ ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍትሕን ያውጃል።
ያጋሩ
ማቴዎስ 12 NASVማቴዎስ 12:18 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
“እነሆ! የመረጥኩት አገልጋዬ ይህ ነው! እርሱ እኔ የምወደውና የምደሰትበት ነው፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ እርሱም ቅን ፍርድን ለሕዝቦች ያውጃል።
ያጋሩ
ማቴዎስ 12 አማ05ማቴዎስ 12:18 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
“እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፤ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።
ማቴዎስ 12:18 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።
ያጋሩ
ማቴዎስ 12 አማ54ማቴዎስ 12:18 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
“እነሆ የመረጥሁት አገልጋዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፤ ፍርድንም ለአሕዛብ ያውጃል።