Skip to content
የBible App ዓርማ

ኢያሱ 7:2 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢያሱ 7:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ኢያሱ ከቤቴል በስተምሥራቅ ካለችው ከቤትአዌን አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ጋይ ከኢያሪኮ ሰዎችን ልኮ፣ “ወደዚያ ውጡ፤ አገሪቱንም ሰልሉ” አላቸው፤ ሰዎቹም ወጥተው ጋይን ሰለሉ።

ኢያሱ 7:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ኢያሱ በኢያሪኮ ሳለ በቤትአዌን አጠገብ ከቤትኤል በስተምሥራቅ የምትገኘውን “ዐይ” ተብላ የምትጠራውን ከተማና የምድሪቱን አቀማመጥ አጥንተው ይመለሱ ዘንድ ጥቂት ሰዎችን ላከ። ይህንንም በትእዛዙ መሠረት ከፈጸሙ በኋላ፥

ኢያሱ 7:2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ኢያ​ሱም ከቤ​ቴል በም​ሥ​ራቅ በኩል በቤ​ት​አ​ዊን አጠ​ገብ ወዳ​ለ​ችው ወደ ጋይ ሰዎ​ችን ከኢ​ያ​ሪኮ ልኮ፥ “ውጡ፤ ጋይ​ንም ሰልሉ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ሰዎ​ቹም ወጡ፤ ጋይ​ንም ሰለሉ።

ኢያሱ 7:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ከኢያሪኮ ልኮ፦ ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ ብሎ ተናገራቸው፥ ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ።

ኢያሱ 7:2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ከኢያሪኮ ላከ፤ እንዲህም አላቸው፦ “ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ፤” ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ።