Skip to content
የBible App ዓርማ

ኢያሱ 2:7 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢያሱ 2:7 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ሰዎቹም ሰላዮቹን በመከታተል ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ የሚወስደውን መንገድ ይዘው ሄዱ፤ አሳዳጆቹ ወጥተው እንደ ሄዱም የቅጥሩ በር ተዘጋ።

ኢያሱ 2:7 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የንጉሡም መልእክተኞች ከከተማይቱ ወጥተው ሄዱ፤ የቅጽር በሩም ተዘጋ፤ መልእክተኞቹም ሰላዮችን በመፈለግ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሮ እስከሚያልፈው ስፍራ ድረስ ሄዱ።

ኢያሱ 2:7 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሰዎ​ቹም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መሻ​ገ​ሪያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ በሩም ተቈ​ለፈ።

ኢያሱ 2:7 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው፥ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተቈለፈ።

ኢያሱ 2:7 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ እስከሚወስደው መንገድ ድረስ አሳደዱአቸው፤ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተዘጋ።