ኢያሱ 2:13 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ኢያሱ 2:13 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
የአባቴንና የእናቴን፣ የወንድሞቼንና የእኅቶቼን እንዲሁም የእነርሱ የሆነውን ነፍስ ሁሉ እንድታተርፉልኝ፤ ከሞትም አድኑን።”
ኢያሱ 2:13 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
አባቴንና እናቴን፥ ወንድሞቼን፥ እኅቶቼንና የእነርሱን ቤተሰቦች ሁሉ ከሞት ለማዳን ቃል ግቡልኝ!”
ኢያሱ 2:13 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
የአባቴን ቤት፥ እናቴንም፥ ወንድሞቼንና ቤቴንም ሁሉ፥ ያላቸውንም ሁሉ አድኑ፤ ሰውነታችንንም ከሞት አድኑ።”
ኢያሱ 2:13 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
አባቴንና እናቴንም ወንድሞቼንና እኅቶቼንም ያላቸውንም ሁሉ እንድታድኑ፥ ሰውነታችንንም ከሞት እንድታድኑ።
ኢያሱ 2:13 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
አባቴንና እናቴንም ወንድሞቼንና እኅቶቼንም ያላቸውንም ሁሉ አድኑ፥ ነፍሳችንንም ከሞት ታደጉ።”