Skip to content

አስቴር 9:3 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

አስቴር 9:3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የየአውራጃው መኳንንት ሁሉ፣ እንደራሴዎች፣ የአውራጃ ገዦች እንዲሁም የንጉሡ አስተዳዳሪዎች አይሁድን ረዷቸው፤ ይህን ያደረጉትም መርዶክዮስን ስለ ፈሩ ነበር።

አስቴር 9:3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እንዲያውም የየሀገሩ ገዢዎችና አስተዳዳሪዎች ሌሎችም ባለሥልጣኖችና የመንግሥት ተወካዮች ሁሉ አይሁድን ረዱአቸው፤ ይህንንም ያደረጉት መርዶክዮስን በመፍራት ነበር።

አስቴር 9:3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

መርዶክዮስን መፍራት በላያቸው ስለ ወደቀ በየአገሩ የነበሩ አዛውንትና ሹማምቶች አለቆችም፥ የንጉሡንም ሥራ የሚሠሩቱ ሁሉ አይሁድን አገዙ።