Skip to content
የBible App ዓርማ

አስቴር 7:2 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

አስቴር 7:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በሁለተኛውም ቀን የወይን ጠጅ እየጠጡ ሳለ፣ ንጉሡ እንደ ገና፣ “ንግሥት አስቴር ሆይ፤ የምትለምኚው ምንድን ነው? ይሰጥሻል፤ የምትጠይቂውስ ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ቢሆን ይደረግልሻል” አላት።

አስቴር 7:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የወይን ጠጅ በመጠጣትም ላይ ሳሉ ንጉሡ “አስቴር ሆይ! ምን እንደምትፈልጊ ንገሪኝ፤ የፈለግሺውን ነገር ሁሉ እፈጽምልሻለሁ፤ የመንግሥቴን እኩሌታ እንኳ ቢሆን እሰጥሻለሁ” ሲል እንደገና ጠየቃት።

አስቴር 7:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በሁለተኛውም ቀን ንጉሡ በወይኑ ጠጅ ግብዣ ሳለ አስቴርን፦ ንግሥት አስቴር ሆይ፥ የምትለምኚኝ ምንድር ነው? ይሰጥሻል፥ የምትሺውስ ምንድር ነው? እስከ መንግሥቴ እኵሌታ እንኳ ቢሆን ይደረግልሻል አላት።