አስቴር 6:4 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
አስቴር 6:4 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ንጉሡም፣ “በአደባባዩ ማን አለ?” ሲል ጠየቀ። በዚህ ጊዜ ሐማ በተከለው ዕንጨት ላይ መርዶክዮስ ይሰቀል ዘንድ ለንጉሡ ለመናገር በውጭ በኩል ወደሚገኘው የቤተ መንግሥቱ አደባባይ ገና መድረሱ ነበር።
ያጋሩ
አስቴር 6 NASVአስቴር 6:4 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ንጉሡም “በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ከባለሥልጣኖቼ መካከል ማን አለ?” ሲል ጠየቀ። በዚህ ጊዜ ሃማን ባዘጋጀው እንጨት ላይ መርዶክዮስን ይሰቅል ዘንድ የንጉሡን ፈቃድ ለመጠየቅ ወደ ቤተ መንግሥቱ አደባባይ በመግባት ላይ ነበር፤
ያጋሩ
አስቴር 6 አማ05አስቴር 6:4 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ንጉሡም፦ በአዳራሹ ማን አለ? አለ። ሐማም ባዘጋጀው ግንድ ላይ መርዶክዮስን ለማሰቀል ለንጉሡ ይናገር ዘንድ ወደ ንጉሡ ቤት ወደ ውጭው አዳራሽ ገብቶ ነበር።
ያጋሩ
አስቴር 6 አማ54