አስቴር 3:7 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

አስቴር 3:7 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ንጉሥ ጠረክሲስ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት ኒሳን በተባለው በመጀመሪያው ወር፣ ቀኑንና ወሩን ለመለየት ፉር የተባለ ዕጣ ሐማ ባለበት ጣሉ፤ ዕጣውም አዳር በተባለው በዐሥራ ሁለተኛው ወር ላይ ወደቀ።

አስቴር 3:7 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

አርጤክስስ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፥ ኒሳን ተብሎ በሚጠራው የመጀመሪያው ወር ፑሪም ተብሎ የተሠየመው ዕጣ መጣል እንዲጀመርና አይሁድን ለማጥፋት የተጠነሰሰውን ሤራ በሥራ ላይ ለማዋል አመቺ የሚሆነው ወርና ቀን የትኛው እንደ ሆነ ተለይቶ እንዲታወቅ ትእዛዝ ሰጠ፤ በዕጣውም መሠረት አዳር ተብሎ የሚጠራው ዐሥራ ሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን እንዲሆን ተወሰነ።

አስቴር 3:7 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በንጉሡም በአርጤክስስ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት ከመጀመሪያው ወር ከኒሳን ጀምሮ በየዕለቱና በየወሩ እስከ አሥራ ሁለተኛው ወር እስከ አዳር ድረስ በሐማ ፊት ፉር የተባለውን ዕጣ ይጥሉ ነበር።