አስቴር 3:4 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
አስቴር 3:4 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ይህንም በየቀኑ ይነግሩት ነበር፤ እርሱ ግን አልተቀበላቸውም። አይሁዳዊ መሆኑን ነግሯቸው ስለ ነበር፣ የመርዶክዮስ ባሕርይ እስከ መቼ ሊቀጥል እንደሚችል ለማየት ሲሉ ይህንኑ ለሐማ ነገሩት።
ያጋሩ
አስቴር 3 NASVአስቴር 3:4 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ከቀን ወደ ቀን ሐሳቡን ለማስቀየር ይጥሩ ነበር፤ እርሱ ግን ሊሰማቸው አልወደደም፤ እንዲያውም እኔ አይሁዳዊ ስለ ሆንኩ ለሃማን መስገድ አይገባኝም በማለት ቊርጥ ውሳኔውን ገለጠላቸው ከዚህ በኋላ የመርዶክዮስን ትዕቢት እንዴት መታገሥ ይቻላል? እያሉ በመገረም ጉዳዩን ለሃማን ነገሩት።
ያጋሩ
አስቴር 3 አማ05አስቴር 3:4 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ይህንም ዕለት ዕለት እየተናገሩ እርሱ ባልሰማቸው ጊዜ አይሁዳዊ እንደ ሆነ ነግሮአቸው ነበርና የመርዶክዮስ ነገር እንዴት እንደ ሆነ ያዩ ዘንድ ለሐማ ነገሩት።
ያጋሩ
አስቴር 3 አማ54