አስቴር 2:18 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
አስቴር 2:18 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ንጉሡም ስለ አስቴር ክብር ለመኳንንቱና ለሹማምቱ ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ በዓሉም በየአውራጃዎቹ ሁሉ እንዲከበር ዐወጀ፤ በንጉሣዊ ልግስናውም ስጦታ አደረገ።
ያጋሩ
አስቴር 2 NASVአስቴር 2:18 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ከዚህም በኋላ ንጉሡ ስለ አስቴር ክብር ታላቅ ግብዣ አዘጋጅቶ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖችና አስተዳዳሪዎች ሁሉ ጠራ፤ በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በሚገኙት አገሮች ሁሉ የደስታ በዓል እንዲደረግ ዐወጀ፤ ለጋስነት የተሞላበት ንጉሣዊ ስጦታም አደረገ።
ያጋሩ
አስቴር 2 አማ05አስቴር 2:18 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ንጉሡም ስለ አስቴር ለባለምዋሎቹና ለአገልጋዮቹ ሁሉ ሰባት ቀን ያህል ትልቅ ግብዣ አደረገ፥ ለአገሮቹም ሁሉ ይቅርታ አደረገ፥ እንደ ንጉሡም ለጋስነት መጠን ስጦታ ሰጠ።
ያጋሩ
አስቴር 2 አማ54