Skip to content
የBible App ዓርማ

አስቴር 2:12 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

አስቴር 2:12 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አንዲት ልጃገረድ ወደ ንጉሥ ጠረክሲስ ዘንድ ለመግባት ተራዋ ከመድረሱ በፊት ስድስት ወር በከርቤ ዘይት፣ ስድስት ወር ደግሞ ልዩ ልዩ ሽቱ በመቀባትና በተለያዩ የፊት ቀለሞች በመዋብ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ወር መቈየት ነበረባት፤

አስቴር 2:12 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሴቶቹ የቊንጅና እንክብካቤ እየተደረገላቸው የሚቆዩት እስከ አንድ ዓመት ነበር፤ ይኸውም የሰውነታቸው ቅርጽ እንዲስተካከል ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በከርቤና በዘይት፥ እንደገናም ለቀሪዎቹ ስድስት ወራት ባልሳም በተባለ ጣፋጭ ሽቶ ይታሻሉ፤ ከዚያም በኋላ እያንዳንድዋ ልጃገረድ በየተራ ወደ ንጉሥ አርጤክስስ ዘንድ እንድትገባ ይደረጋል።

አስቴር 2:12 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

የመንጻታቸውም ወራት ስድስት ወር ያህል በከርቤ ዘይት፥ ስድስት ወርም በጣፋጭ ሽቱና በልዩ ልዩም በሚያነጻ ነገር ይፈጸም ነበርና እንደ ሴቶች ወግ አሥራ ሁለት ወር እንዲሁ ከተደረገላት በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ አርጤክስስ ለመግባት የአንዳንዲቱ ቆንጆ ተራ በደረሰ ጊዜ፥