ሐዋርያት ሥራ 9:8 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 9:8 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ሳውልም ከመሬት ላይ ተነሥቶ ዐይኑን ሲገልጥ ምንም ማየት አልቻለም፤ ስለዚህ ሰዎቹ እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አስገቡት።
ሐዋርያት ሥራ 9:8 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ሳውልም ከወደቀበት መሬት ተነሣ፤ ዐይኖቹን በገለጠ ጊዜ ግን ምንም ማየት አልቻለም፤ ስለዚህ ሰዎቹ እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ ወሰዱት።
ሐዋርያት ሥራ 9:8 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ሳውልም ከምድር ተነሣ፤ ነገር ግን ዐይኖቹ ተገልጠው ሳሉ የሚያየው ነገር አልነበረም፤ እየመሩም ወደ ደማስቆ አገቡት።
ሐዋርያት ሥራ 9:8 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ሳውልም ከምድር ተነሣ፥ አይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አገቡት።
ሐዋርያት ሥራ 9:8 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ሳውልም ከምድር ተነሣ፤ ዐይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አገቡት።