ሐዋርያት ሥራ 9:26 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 9:26 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ፣ ከደቀ መዛሙርት ጋራ ለመቀላቀል ሞከረ፤ እነርሱ ግን በርግጥ ደቀ መዝሙር መሆኑን ስላላመኑ ሁሉም ፈሩት።
ሐዋርያት ሥራ 9:26 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ሳውል ወደ ኢየሩሳሌም በሄደ ጊዜ እዚያ ካሉት ደቀ መዛሙርት ጋር ለመደባለቅ ሞከረ፤ እነርሱ ግን የእርሱ በክርስቶስ ማመን እውነት ስላልመሰላቸው ሁሉም ፈሩት።
ሐዋርያት ሥራ 9:26 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ሊገናኛቸው ደቀ መዛሙርትን ፈለጋቸው። ሁሉም ፈሩት፤ የጌታችን ደቀ መዝሙር እንደ ሆነ አላመኑትም ነበርና።
ሐዋርያት ሥራ 9:26 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርት ጋር ይተባበር ዘንድ ሞከረ፤ ሁሉም ደቀ መዝሙር እንደ ሆነ ስላላመኑ ፈሩት።
ሐዋርያት ሥራ 9:26 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርት ጋር ይተባበር ዘንድ ሞከረ፤ ሁሉም ደቀመዝሙር እንደሆነ ስላላመኑ ፈሩት።