Skip to content

ሐዋርያት ሥራ 8:27 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 8:27 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እርሱም ተነሥቶ ሄደ። እነሆ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ ባለሟልና የሀብት ንብረቷ ሁሉ አዛዥ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አገኘ። ይህም ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 8:27 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እርሱም ተነሥቶ ሄደ፤ እነሆ፥ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ለእግዚአብሔር ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤ ይህ ሰው ሕንደኬ ለተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሟልና የገንዘብዋ ሁሉ ኀላፊ ነበረ።

ሐዋርያት ሥራ 8:27 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ሥት የሕ​ን​ደኬ ጃን​ደ​ረባ ከሹ​ሞ​ችዋ የበ​ለጠ፥ በሀ​ብ​ቷም ሁሉ ላይ በጅ​ሮ​ንድ የነ​በረ፥ አንድ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ሊሰ​ግድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ።

ሐዋርያት ሥራ 8:27 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤

ሐዋርያት ሥራ 8:27 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ሕንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሥልጣን የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ ኀላፊ አንድ ኢትዮጵያ ጃንደረባ ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤