Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 7:8 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 7:8 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚያም የግዝረትን ኪዳን ሰጠው፤ አብርሃምም ይሥሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው። ይሥሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የነገድ አባቶች ወለደ።

ሐዋርያት ሥራ 7:8 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ ስለዚህ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ እንዲሁም ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ገረዘው። ያዕቆብም የነገድ አባቶች የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን ልጆቹን ገረዘ።

ሐዋርያት ሥራ 7:8 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የግ​ዝ​ረ​ት​ንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚ​ህም በኋላ ይስ​ሐ​ቅን ወለደ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀንም ገረ​ዘው፤ እን​ዲሁ ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን፥ ያዕ​ቆ​ብም ዐሥራ ሁለ​ቱን የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችን ገረዙ።

ሐዋርያት ሥራ 7:8 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም አሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች።

ሐዋርያት ሥራ 7:8 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች።