Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 7:42 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 7:42 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ ዘወር አለ፤ ያመልኳቸውም ዘንድ ለሰማይ ከዋክብት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም በነቢያት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ በተጻፈው መሠረት ተፈጸመ፤ “ ‘እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፤ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣ መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን?

ሐዋርያት ሥራ 7:42 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እግዚአብሔር ግን ተለያቸው። የሰማይንም ከዋክብት እንዲያመልኩ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም በነቢያት እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፤ ‘እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ! የታረደውን እንስሳና መሥዋዕትን አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ያቀረባችሁት ለእኔ ነውን?

ሐዋርያት ሥራ 7:42 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተለ​ያ​ቸው፤ የሰ​ማይ ጭፍ​ራን ያመ​ል​ኩም ዘንድ ተዋ​ቸው፤ የነ​ቢ​ያት መጽ​ሐፍ እን​ዲህ እን​ዳለ፤ ‘እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ በውኑ በም​ድረ በዳ ሳላ​ችሁ አርባ ዐመት ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​ልኝ ቍር​ባ​ንና መሥ​ዋ​ዕት አለን?

ሐዋርያት ሥራ 7:42 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው፥ በነቢያትም መጽሐፍ፦ ‘እናንተ የእስራኤል ቤት፥ አርባ ዓመት በምድረ በዳ የታረደውን ከብትና መሥዋዕትን አቀረባችሁልኝን?

ሐዋርያት ሥራ 7:42 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ፤ የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው፤ በነቢያትም መጽሐፍ ‘እናንተ የእስራኤል ቤት! አርባ ዓመት በምድረ በዳ የታረደውን ከብትና መሥዋዕትን አቀረባችሁልኝን?