ሐዋርያት ሥራ 7:40 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 7:40 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
አሮንንም፣ ‘በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንዳገኘው አናውቅምና!’ አሉት።
ሐዋርያት ሥራ 7:40 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
አሮንንም ‘ይህ ከግብጽ አገር ያወጣን ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅምና እፊት እፊታችን እየሄዱ የሚመሩንን አማልክት ሥራልን’ አሉት።
ሐዋርያት ሥራ 7:40 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
አሮንንም፦ ‘በፊት በፊታችን የሚሄዱ አማልክትን ሥራልን፤ ያ ከምድረ ግብፅ ያወጣን ሙሴ የሆነውን አናውቅምና’ አሉት።
ሐዋርያት ሥራ 7:40 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
አሮንንም፦ ‘በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና’ አሉት።
ሐዋርያት ሥራ 7:40 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
አሮንንም ‘በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ይህ ከግብጽ ምድር ያወጣን ሙሴ ምን እንደሆነ አናውቅምና፤’ አሉት።