ሐዋርያት ሥራ 7:37 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 7:37 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“የእስራኤልንም ልጆች፣ ‘እግዚአብሔር እንደ እኔ ያለ ነቢይ ከወንድሞቻችሁ መካከል ያስነሣላችኋል’ ያላቸው ይኸው ሙሴ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 7:37 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
‘ጌታ አምላካችሁ እኔን እንዳስነሣኝ እንዲሁ ከወንድሞቻችሁ መካከል ነቢይ ያስነሣላችኋል’ ብሎ ለእስራኤላውያን የተናገረው ይኸው ሙሴ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 7:37 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ለእስራኤልም ልጆች፦ ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋልና እርሱን ስሙት’ ያላቸው ይህ ሙሴ ነው።
ሐዋርያት ሥራ 7:37 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ይህ ሰው ለእስራኤል ልጆች፦ ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት’ ያላቸው ሙሴ ነው።
ሐዋርያት ሥራ 7:37 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ይህ ሰው ለእስራኤል ልጆች ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት፤’ ያላቸው ሙሴ ነው።