Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 7:30 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 7:30 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“ከአርባ ዓመት በኋላ፣ በሲና ተራራ አካባቢ ባለው ምድረ በዳ፣ በቍጥቋጦው ውስጥ በሚንቀለቀል የእሳት ነበልባል መልአክ ተገለጠለት።

ሐዋርያት ሥራ 7:30 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“ሙሴ በዚያ አገር አርባ ዓመት ካሳለፈ በኋላ በደብረ ሲና በረሓ በሚነደው የቊጥቋጦ ነበልባል ውስጥ አንድ መልአክ ታየው።

ሐዋርያት ሥራ 7:30 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“አርባ ዓመ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በበ​ረሃ በደ​ብረ ሲና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በቍ​ጥ​ቋጦ መካ​ከል በእ​ሳት ነበ​ል​ባል ታየው።

ሐዋርያት ሥራ 7:30 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አርባ ዓመትም ሲሞላ የጌታ መልአክ በሲና ተራራ ምድረ በዳ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው።

ሐዋርያት ሥራ 7:30 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“አርባ ዓመትም ሲሞላ የጌታ መልአክ በሲና ተራራ ምድረ በዳ በቁጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው።