ሐዋርያት ሥራ 7:27 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 7:27 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“በባልንጀራው ላይ በደል ሲያደርስ የነበረው ሰው ግን፣ ሙሴን ገፈተረውና እንዲህ አለ፤ ‘አንተን በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው?
ሐዋርያት ሥራ 7:27 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ያ ባልንጀራውን ይደበድብ የነበረው ሰው ሙሴን ወዲያ ገፈተረና ‘አንተን በእኛ ላይ ገዢና ፈራጅ ያደረገህ ማን ነው?
ሐዋርያት ሥራ 7:27 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ያም ባልንጀራውን የሚበድለው ገፋው፤ እንዲህም አለው፦ ‘አንተን በእኛ ላይ ዳኛና ፈራጅ አድርጎ ማን ሾመህ?
ሐዋርያት ሥራ 7:27 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ያም ባልንጀራውን የሚበድል ግን፦ ‘አንተን በእኛ ላይ ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው?
ሐዋርያት ሥራ 7:27 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ያም ባልንጀራውን የሚበድል ግን ‘አንተን በእኛ ላይ ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው?