ሐዋርያት ሥራ 7:20 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 7:20 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“በዚህ ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ያገኘ ውብ ሕፃን ነበር። በአባቱም ቤት ሦስት ወር በእንክብካቤ አደገ።
ሐዋርያት ሥራ 7:20 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
በዚያን ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ያማረ ሕፃን ነበር፤ ሦስት ወር በአባቱ ቤት አደገ፤
ሐዋርያት ሥራ 7:20 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
“ያንጊዜም ሙሴ ተወለደ፤ በእግዚአብሔር ፊትም የተወደደ ሆነ፤ ለሦስት ወርም በአባቱ ቤት አሳደጉት።
ሐዋርያት ሥራ 7:20 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
በዚያን ጊዜ ሙሴ ተወለደ በእግዚአብሔርም ፊት ያማረ ነበር፤ በአባቱ ቤትም ሦስት ወር አደገ፤
ሐዋርያት ሥራ 7:20 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
በዚያን ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ያማረ ነበር፤ በአባቱ ቤትም ሦስት ወር አደገ፤