ሐዋርያት ሥራ 6:11 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 6:11 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ስለዚህ፣ “እስጢፋኖስ በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲሰነዝር ሰምተናል” የሚሉ ሰዎችን በስውር አዘጋጁ።
ሐዋርያት ሥራ 6:11 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
በዚያን ጊዜ “ይህ ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተነዋል” የሚሉ ሰዎችን በስውር አነሣሡበት።
ሐዋርያት ሥራ 6:11 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ከዚህም በኋላ “ይህን ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል” የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አስነሡበት፤
ሐዋርያት ሥራ 6:11 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
በዚያን ጊዜ፦ “በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል” የሚሉ ሰዎችን አስነሡ።
ሐዋርያት ሥራ 6:11 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
በዚያን ጊዜ “በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል፤” የሚሉ ሰዎችን አስነሡ።