Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 5:36 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 5:36 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚህ ቀደም፣ ቴዎዳስ ራሱን ትልቅ አድርጎ በመቍጠር ተነሥቶ፣ አራት መቶ ያህል ሰዎች ተባበሩት፤ ነገር ግን እርሱም ተገደለ፤ ተከታዮቹም ሁሉ ተበታተኑ፤ ነገሩም እንዳልነበር ሆነ።

ሐዋርያት ሥራ 5:36 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከዚህ በፊት ቴዎዳስ የሚባል ሰው ‘እኔ ትልቅ ሰው ነኝ’ ብሎ ተነሥቶ ነበር፤ አራት መቶ የሚያኽሉም ሰዎች ከእርሱ ጋር ተባብረው ነበር። ነገር ግን እርሱ ተገደለ፤ ተከታዮቹ ተበታተኑ፤ ዓላማውም እንዳልነበረ ሆነ።

ሐዋርያት ሥራ 5:36 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ቀድ​ሞም ከዚህ ዘመን በፊት ቴዎ​ዳስ ተነ​ሥቶ ራሱን ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ አራት መቶ ሰዎ​ችም ተከ​ተ​ሉት፤ ነገር ግን እር​ሱም ጠፋ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​ትም ሁሉ ተበ​ታ​ተኑ፤ እንደ ኢም​ን​ትም ሆኑ።

ሐዋርያት ሥራ 5:36 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ፦ “እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፥ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ።

ሐዋርያት ሥራ 5:36 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ ‘እኔ ታላቅ ነኝ፤’ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፤ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ፤ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ፤ እንደ ምናምንም ሆኑ።