Skip to content

ሐዋርያት ሥራ 5:15 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 5:15 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚህም የተነሣ፣ ጴጥሮስ በዚያ ሲያልፍ፣ ቢያንስ ጥላው እንኳ በጥቂቶች ላይ እንዲያርፍባቸው በማለት ሕመምተኞችን ወደ ውጭ እያወጡ በዐልጋና በቃሬዛ በመንገድ ላይ ያስተኙ ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 5:15 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሰዎች ብዙ በሽተኞችን ወደ መንገድ እያወጡ በአልጋ ላይና በቃሬዛ ላይ ያስተኙአቸው ነበር፤ እንዲህም ያደረጉት ጴጥሮስ በዚያ በኩል ሲያልፍ ጥላው እንኳ በአንዳንዶቹ ላይ እንዲያርፍባቸው ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 5:15 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ጴጥ​ሮ​ስም አልፎ ሲሄድ ጥላው ያር​ፍ​ባ​ቸው ዘንድ ድው​ዮ​ችን በአ​ል​ጋና በቃ​ሬዛ እያ​መጡ በአ​ደ​ባ​ባይ ያስ​ቀ​ም​ጡ​አ​ቸው ነበር፤

ሐዋርያት ሥራ 5:15 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 5:15 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።