ሐዋርያት ሥራ 4:9 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 4:9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ዛሬ ለዚህ ሽባ ሰው ስለ ተደረገው በጎ ሥራ፣ እንዴት እንደ ዳነ የምትጠይቁን ከሆነ፣

ሐዋርያት ሥራ 4:9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እኛ ዛሬ የምንጠየቀው ለአንድ ሽባ ሰው ስለ ተደረገለት መልካም ሥራና በምን ዐይነት ሁኔታ እንደ ዳነ ነው።

ሐዋርያት ሥራ 4:9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ዛሬ ለበ​ሽ​ተ​ኛው በተ​ደ​ረ​ገው ረድ​ኤት ምክ​ን​ያት በእ​ና​ንተ ዘንድ እኛ የሚ​ፈ​ረ​ድ​ብን ከሆነ እን​ግ​ዲያ ይህ ሰው በምን ዳነ?

ሐዋርያት ሥራ 4:9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለ ተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደዳነ ብንመረመር፥

ሐዋርያት ሥራ 4:9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደ ዳነ ብንመረመር፥