ሐዋርያት ሥራ 4:5 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 4:5 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
በማግስቱም አለቆቻቸውና፣ ሽማግሌዎቻቸው እንዲሁም ጸሐፍት በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።
ሐዋርያት ሥራ 4:5 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
በማግስቱ የአይሁድ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ የሕግ መምህራንም በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።
ሐዋርያት ሥራ 4:5 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
በማግሥቱም አለቆቻቸውና ሽማግሎች፥ ጻፎችም በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።
ሐዋርያት ሥራ 4:5-6 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
በነገውም አለቆቻቸውና ሽማግሌዎች ጻፎችም ሊቀ ካህናቱ ሐናም ቀያፋም ዮሐንስም እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤
ሐዋርያት ሥራ 4:5-6 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
በነገውም አለቆቻቸውና ሽማግሌዎች ጻፎችም ሊቀ ካህናቱ ሐናም ቀያፋም ዮሐንስም እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤