ሐዋርያት ሥራ 4:2 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 4:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
እነርሱም ሐዋርያት ሕዝቡን በማስተማራቸውና በኢየሱስ ስለ ተገኘው ትንሣኤ ሙታን በመስበካቸው እጅግ ተቈጡ።
ሐዋርያት ሥራ 4:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ሁለቱ ሐዋርያት የኢየሱስን ከሞት መነሣት ለሕዝቡ በማስተማራቸውና በዚህም የሙታን ትንሣኤ መኖሩን በማስረዳታቸው ተቈጡ።
ሐዋርያት ሥራ 4:2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ሕዝቡን ስለ አስተማሩና በኢየሱስም የሙታንን ትንሣኤ ስለ ሰበኩ በእነርሱ ተናደዱ።
ሐዋርያት ሥራ 4:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ሕዝቡን ስለ አስተማሩና በኢየሱስ የሙታንን ትንሣኤ ስለ ሰበኩ ተቸግረው፥ ወደ እነርሱ ቀረቡ፥
ሐዋርያት ሥራ 4:2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ሕዝቡን ስለ አስተማሩና በኢየሱስ የሙታንን ትንሣኤ ስለ ሰበኩ እጅግም ተቆጥተው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤