Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 3:11 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 3:11 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የተፈወሰውም ሰው ከጴጥሮስና ዮሐንስ ጋራ ጥብቅ ብሎ ዐብሯቸው ሳለ፣ ሕዝቡ ሁሉ በመገረም እነርሱ ወደ ነበሩበት “የሰሎሞን መመላለሻ” ወደተባለው ስፍራ እየሮጡ መጡ።

ሐዋርያት ሥራ 3:11 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የዳነው ሰው ከጴጥሮስና ከዮሐንስ አልለይም በማለት ይዞአቸው ሳለ ሰዎቹ ተደንቀው “የሰሎሞን መመላለሻ” ወደሚባለው ስፍራ ወደ እነርሱ ሮጠው ሄዱ፤

ሐዋርያት ሥራ 3:11 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ይዘ​ውት ወደ መቅ​ደስ ሲገቡ ሕዝቡ ሁሉ ደን​ግ​ጠው ወደ ሰሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ ወደ እነ​ርሱ ሮጡ።

ሐዋርያት ሥራ 3:11 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ።

ሐዋርያት ሥራ 3:11 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ።