ሐዋርያት ሥራ 28:2 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 28:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የደሴቲቱ ነዋሪዎችም የሚያስገርም ደግነት አሳዩን፤ ዝናብና ብርድ ነበርና እሳት አንድደው ሁላችንን ተቀበሉን።

ሐዋርያት ሥራ 28:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የዚያች ደሴት ነዋሪዎች የሚያስደንቅ ደግነት አደረጉልን፤ በዚያን ጊዜም ዝናብ ስለ ዘነበና ብርድ ስለ ሆነ እሳት አንድደው ተቀበሉን፤

ሐዋርያት ሥራ 28:2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በዚያ የሚ​ኖ​ሩት አረ​ማ​ው​ያ​ንም አዘ​ኑ​ልን፤ መል​ካም ነገ​ር​ንም አደ​ረ​ጉ​ልን፤ ከቍ​ሩም ጽና​ትና ከዝ​ናሙ ብዛት የተ​ነሣ እሳት አን​ድ​ደው እን​ድ​ን​ሞቅ ሁላ​ች​ን​ንም ሰበ​ሰ​ቡን።

ሐዋርያት ሥራ 28:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አረማውያንም የሚያስገርም ቸርነት አደረጉልን፤ ዝናብ ስለ ሆነም ስለ ብርዱም እሳት አንድደው ሁላችንን ተቀበሉን።

ሐዋርያት ሥራ 28:2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አረማውያንም የሚያስገርም ቸርነት አደረጉልን፤ ዝናብ ስለ ሆነም ስለ ብርዱም እሳት አንድደው ሁላችንን ተቀበሉን።