ሐዋርያት ሥራ 27:7 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 27:7 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ብዙ ቀን በዝግታ እየተጓዝን ቀኒዶስ አካባቢ በጭንቅ ደረስን፤ ነፋሱም ወደ ፊት እንዳንሄድ በከለከለን ጊዜ፣ በሰልሙና አጠገብ አድርገን በቀርጤስ ተተግነን ሄድን፤
ሐዋርያት ሥራ 27:7 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ብዙ ቀን ቀስ እያልን ተጒዘን በብዙ ችግር ወደ ቀኒዶስ ከተማ አጠገብ ደረስን፤ ነፋሱም ወደፊት እንዳንሄድ ስለ ከለከለን በሰልሞና ርእሰ ምድር ጫፍ አጠገብ አለፍንና የቀርጤስን ደሴት ተገን አድርገን ሄድን።
ሐዋርያት ሥራ 27:7 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ብዙ ቀንም እያዘገምን ሄድን፤ በጭንቅም ወደ ቀኒዶስ አንጻር ደረስን፤ ወደዚያም በቀጥታ ለመድረስ ነፋስ ቢከለክለን በቀርጤስ በኩል በሰልሙና ፊት ለፊት ዐለፍን።
ሐዋርያት ሥራ 27:7 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ብዙ ቀንም እያዘገምን ሄደን በጭንቅ ወደ ቀኒዶስ አንጻር ደረስን፤ ነፋስም ስለ ከለከለን በቀርጤስ ተተግነን በሰልሙና አንጻር ሄድን፤
ሐዋርያት ሥራ 27:7 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ብዙ ቀንም እያዘገምን ሄደን በጭንቅ ወደ ቀኒዶስ አንጻር ደረስን፤ ነፋስም ስለ ከለከለን በቀርጤስ ተተግነን በሰልሙና አንጻር ሄድን፤