Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 26:31 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 26:31 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ወጥተውም ሲሄዱ፣ “ይህ ሰው እንኳን ለሞት፣ ለእስራት የሚያበቃው ነገር አላደረገም” ተባባሉ።

ሐዋርያት ሥራ 26:31 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከዚያም ወጥተው ሲሄዱ፥ “ይህ ሰው ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃው ምንም ነገር አላደረገም” ተባባሉ።

ሐዋርያት ሥራ 26:31 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ለብ​ቻ​ቸ​ውም ገለል ብለው እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ብለው ተነ​ጋ​ገሩ፥ “ይህ ሰው እን​ዲ​ሞት ወይም እን​ዲ​ታ​ሰር የሚ​ያ​በቃ የሠ​ራው በደል የለም።”

ሐዋርያት ሥራ 26:31 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ፈቀቅ ብለውም እርስ በርሳቸው፦ “ይህ ሰው እንኳንስ ለሞት ለእስራትም የሚገባ ምንም አላደረገ ብለው ተነጋገሩ።

ሐዋርያት ሥራ 26:31 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ፈቀቅ ብለውም እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው እንኳንስ ለሞት ለእስራትም የሚገባ ምንም አላደረገ፤” ብለው ተነጋገሩ።