Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 26:1 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 26:1 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አግሪጳም ጳውሎስን፣ “ስለ ራስህ እንድትናገር ተፈቅዶልሃል” አለው። በዚህ ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ እንዲህ ሲል መከላከያውን አቀረበ፤

ሐዋርያት ሥራ 26:1 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

አግሪጳ ጳውሎስን “ስለ ራስህ እንድትናገር ተፈቅዶልሃል” አለው፤ ጳውሎስም እጁን ዘረጋና እንዲህ ሲል የመከላከያ መልሱን ሰጠ።

ሐዋርያት ሥራ 26:1 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

አግ​ሪ​ጳም ጳው​ሎ​ስን፥ “ስለ ራስህ ትና​ገር ዘንድ ፈቅ​ደ​ን​ል​ሃል” አለው፤ ከዚ​ህም በኋላ ጳው​ሎስ እጁን አነ​ሣና ይነ​ግ​ራ​ቸው ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦

ሐዋርያት ሥራ 26:1 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አግሪጳም ጳውሎስን፦ “ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ተፈቅዶልሃል” አለው። በዚያን ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ መለሰ እንዲህ ሲል፦

ሐዋርያት ሥራ 26:1 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አግሪጳም ጳውሎስን “ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ተፈቅዶልሃል፤” አለው። በዚያን ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ እንዲህ ሲል መለሰ፦