ሐዋርያት ሥራ 25:4 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 25:4 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ፊስጦስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ጳውሎስ ታስሮ በቂሳርያ እስር ቤት ይገኛል፤ እኔም በቅርቡ ወደዚያው እሄዳለሁ።
ሐዋርያት ሥራ 25:4 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ፊስጦስ ግን “ጳውሎስ በቂሳርያ በእስር ቤት እየተጠበቀ ነው፤ እኔም አሁን በቶሎ ተመልሼ ወደዚያ እሄዳለሁ፤
ሐዋርያት ሥራ 25:4 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ፊስጦስም ጳውሎስን በቂሣርያ እንደሚጠብቁት፥ እርሱም ራሱ ወደዚያው በቶሎ እንደሚሄድ መለሰላቸው።
ሐዋርያት ሥራ 25:4 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ፊስጦስ ግን ጳውሎስ በቂሳርያ እንዲጠበቅ እርሱም ራሱ ወደዚያ ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ እንዳለው መለሰላቸው፤
ሐዋርያት ሥራ 25:4 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ፊስጦስ ግን ጳውሎስ በቂሳርያ እንዲጠበቅ እርሱም ራሱ ወደዚያ ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ እንዳለው መለሰላቸው፤