Skip to content

ሐዋርያት ሥራ 25:23 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 25:23 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በማግስቱም አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ክብር መጥተው፣ ከከፍተኛ መኰንኖችና ከከተማዪቱ ታላላቅ ሰዎች ጋራ ወደ መሰብሰቢያው አዳራሽ ገቡ፤ በፊስጦስም ትእዛዝ ጳውሎስ እንዲቀርብ ተደረገ።

ሐዋርያት ሥራ 25:23 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ስለዚህ በማግስቱ አግሪጳና በርኒቄ ልብሰ መንግሥታቸውን ለብሰውና በታላቅ ግርማ ሆነው በጦር አለቆችና በከተማው ታላላቅ ሰዎችም ታጅበው መጡና ወደ ፍርድ አዳራሽ ገቡ፤ ከዚያም በኋላ ፊስጦስ ጳውሎስን አስጠራ።

ሐዋርያት ሥራ 25:23 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በማ​ግ​ሥ​ቱም አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ በብዙ ግርማ መጡ፤ ከመ​ሳ​ፍ​ን​ቱና ከከ​ተ​ማው ታላ​ላቅ ሰዎች ጋርም ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስ​ጦ​ስም ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ።

ሐዋርያት ሥራ 25:23 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በነገውም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጥተው ከሻለቆችና ከከተማው ታላላቆች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስን አመጡት።

ሐዋርያት ሥራ 25:23 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በነገውም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጥተው ከሻለቆችና ከከተማው ታላላቆች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስን አመጡት።