Skip to content

ሐዋርያት ሥራ 24:12 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 24:12 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከሳሾቼም በቤተ መቅደስ ከማንም ጋራ ስከራከር ወይም በምኵራብ ወይም በከተማ ውስጥ በየትኛውም ስፍራ ሕዝብን ሳነሣሣ አላገኙኝም።

ሐዋርያት ሥራ 24:12 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በቤተ መቅደስም ሆነ በምኲራብ ወይም በከተማ ውስጥ ከማንም ጋር ስከራከር ወይም ሕዝቡን ለሁከት ሳነሣሣ አላገኙኝም፤

ሐዋርያት ሥራ 24:12 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በም​ኵ​ራብ ቢሆን፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ቢሆን፥ በከ​ተ​ማም ቢሆን ሕዝ​ብን ሳውክ፥ ከማ​ንም ጋር ስከ​ራ​ከር አላ​ገ​ኙ​ኝም።

ሐዋርያት ሥራ 24:12 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ከአንድም ስንኳ ስነጋገር ወይም ሕዝብን ስሰበስብ በመቅደስ ቢሆን በምኵራብም ቢሆን በከተማም ቢሆን አላገኙኝም።

ሐዋርያት ሥራ 24:12 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከአንድም ስንኳ ስነጋገር ወይም ሕዝብን ስሰበስብ በመቅደስ ቢሆን በምኵራብም ቢሆን በከተማም ቢሆን አላገኙኝም።