Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 23:3 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 23:3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ጳውሎስም፣ “አንተ በኖራ የተለሰንህ ግድግዳ! እግዚአብሔር ደግሞ አንተን ይመታሃል፤ በሕጉ መሠረት ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ፣ ያለ ሕግ ስላስመታኸኝ አንተ ራስህ ሕጉን ጥሰሃል” አለው።

ሐዋርያት ሥራ 23:3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በዚህ ጊዜ ጳውሎስ ሐናንያን፥ “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳን የምትመስል! አንተንም እግዚአብሔር ይመታሃል! በሕግ መሠረት የእኔን ጉዳይ ልትፈርድ ተቀምጠህ ሳለ ያለ ሕግ እንዲመቱኝ ታዛለህን?”

ሐዋርያት ሥራ 23:3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ጳው​ሎ​ስም መልሶ፥ “አንተ የተ​ለ​ሰነ ግድ​ግዳ በሕግ ልት​ፈ​ር​ድ​ብኝ ተቀ​ም​ጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝ​ዛ​ለ​ህን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ሃል” አለው።

ሐዋርያት ሥራ 23:3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በዚያን ጊዜ ጳውሎስ፦ አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ፥ እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን? አለው።

ሐዋርያት ሥራ 23:3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በዚያን ጊዜ ጳውሎስ “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ! እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን?” አለው።