ሐዋርያት ሥራ 23:24 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 23:24 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ደግሞም ጳውሎስ ተቀምጦበት ወደ አገረ ገዥው ወደ ፊልክስ በደኅና የሚደርስበት ከብት ይዘጋጅ።”
ሐዋርያት ሥራ 23:24 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ለጳውሎስም ፈረስ አዘጋጁለትና ወደ አገረ ገዥው ወደ ፊልክስ በደኅና እንዲደርስ አድርጉት” አላቸው።
ሐዋርያት ሥራ 23:24 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
አህያም አምጥተው ጳውሎስን በዚያ አስቀምጠው ወደ ቂሣርያ አገረ ገዢ ወደ ፊልክስ እንዲወስዱት አዘዛቸው።
ሐዋርያት ሥራ 23:24 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ጳውሎስንም ወደ አገረ ገዡ ወደ ፊልክስ በደኅና እንዲያደርሱት የሚያስቀምጡበትን ከብት ያዘጋጁ ዘንድ አዘዛቸው።
ሐዋርያት ሥራ 23:24 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ጳውሎስንም ወደ አገረ ገዢው ወደ ፊልክስ በደኅና እንዲያደርሱት የሚያስቀምጡበትን ከብት ያዘጋጁ ዘንድ አዘዛቸው።