ሐዋርያት ሥራ 22:8 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 22:8 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፤ አንተ ማን ነህ?’ አልሁት። “እርሱም፣ ‘አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ’ አለኝ።
ሐዋርያት ሥራ 22:8 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
እኔም ‘ጌታ ሆይ! አንተ ማን ነህ?’ አልኩ፤ እርሱም ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ’ አለኝ።
ሐዋርያት ሥራ 22:8 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
እኔም መልሼ፦ ‘አቤቱ፥ አንተ ማነህ?’ አልሁት፤ እርሱም፦ ‘አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ’ አለኝ።
ሐዋርያት ሥራ 22:8 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
እኔም መልሼ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ? አልሁ። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ እኔ ነኝ አለኝ።
ሐዋርያት ሥራ 22:8 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
እኔም መልሼ ‘ጌታ ሆይ! አንተ ማን ነህ?’ አልሁ። እርሱም ‘አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ እኔ ነኝ፤’ አለኝ።