Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 22:3 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 22:3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“እኔ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ የተወለድሁ አይሁዳዊ ስሆን፣ ያደግሁት ግን በዚህ ከተማ ነው። የአባቶቻችንን ሕግ በገማልያል እግር ሥር ተቀምጬ በሚገባ ተምሬአለሁ፤ ዛሬ እናንተ እንዲህ የምትቀኑለትን ያህል እኔም ለእግዚአብሔር እቀና ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 22:3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“እኔ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ ከተማ የተወለድኩ አይሁዳዊ ነኝ፤ ያደግኹት ግን በዚህች በኢየሩሳሌም ከተማ ነው። አስተማሪዬም ገማልያል ነበር፤ የአባቶችን ሕግ ጠንቅቄ የተማርኩና ልክ ዛሬ እናንተ እንደምታደርጉት እግዚአብሔርን በመንፈሳዊ ቅናት የማገለግል ነበርኩ።

ሐዋርያት ሥራ 22:3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ነኝ፤ የቂ​ል​ቅያ ክፍል በም​ት​ሆን በጠ​ር​ሴስ ከተማ ተወ​ለ​ድሁ፤ በዚ​ችም ከተማ ከገ​ማ​ል​ያል እግር ሥር ሆኜ አደ​ግሁ፤ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም ሕግ ተማ​ርሁ፤ እና​ንተ ሁላ​ችሁ ዛሬ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀና​ተኛ ነበ​ርሁ።

ሐዋርያት ሥራ 22:3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እኔ የኪልቅያ በምትሆን በጠርሴስ የተወለድሁ፥ በዚችም ከተማ በገማልያል እግር አጠገብ ያደግሁ፥ የአባቶችንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ፥ ዛሬውንም እናንተ ሁሉ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ አይሁዳዊ ሰው ነኝ

ሐዋርያት ሥራ 22:3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“እኔ የኪልቅያ በምትሆን በጠርሴስ የተወለድሁ፥ በዚችም ከተማ በገማልያል እግር አጠገብ ያደግሁ፥ የአባቶችንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ፥ ዛሬውንም እናንተ ሁሉ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ አይሁዳዊ ሰው ነኝ።