Skip to content

ሐዋርያት ሥራ 21:3 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 21:3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ቆጵሮስ በታየችን ጊዜ፣ ወደ ግራ ትተናት ዐለፍንና ወደ ሶርያ አመራን፤ መርከባችን ጭነቱን በጢሮስ ማራገፍ ስለ ነበረበት እኛም እዚያው ወረድን።

ሐዋርያት ሥራ 21:3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የቆጵሮስን ደሴት በስተግራችን ትተን ወደ ሶርያ አገር ተጓዝንና ወደ ጢሮስ ወደብ ሄድን፤ መርከቡ ጭነቱን እዚያ ማራገፍ ነበረበት።

ሐዋርያት ሥራ 21:3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ቆጵ​ሮ​ስ​ንም አየ​ናት፤ በስተ ግራ​ች​ንም ትተ​ናት ወደ ሶርያ ሄድን፤ ወደ ጢሮ​ስም ወረ​ድን፤ በመ​ር​ከብ ያለ​ውን ጭነት ሁሉ በዚያ ያራ​ግፉ ነበ​ርና።

ሐዋርያት ሥራ 21:3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ቆጵሮስንም ባየናት ጊዜ በስተ ግራችን ተውናት ወደ ሶርያም ሄደን ወደ ጢሮስ ደረስን፥ መርከቡ ሸክሙን በዚያ የሚያራግፍ ነበርና።

ሐዋርያት ሥራ 21:3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ቆጵሮስንም ባየናት ጊዜ በስተ ግራችን ተውናት፤ ወደ ሶርያም ሄደን ወደ ጢሮስ ደረስን፤ መርከቡ ሸክሙን በዚያ የሚያራግፍ ነበርና።