Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 2:6 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 2:6 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ይህን ድምፅ ሲሰሙ፣ ብዙ ሕዝብ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ እያንዳንዱም ሰው፣ ሰዎቹ በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ በመስማቱ ግራ ተጋባ፤

ሐዋርያት ሥራ 2:6 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ይህንንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ በየቋንቋቸውም ሲናገሩ ስለ ሰሙአቸው ተደነቁ።

ሐዋርያት ሥራ 2:6 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ይህ​ንም ቃል ሲና​ገሩ ሰም​ተው ሁሉም ደን​ግ​ጠው ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሁሉም በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ቋንቋ ሲና​ገሩ ሰም​ተ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና የሚ​ሉ​ትን አጡ።

ሐዋርያት ሥራ 2:6 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ።

ሐዋርያት ሥራ 2:6 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ።