Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 19:8 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 19:8 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ጳውሎስም ወደ ምኵራብ እየገባ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተነጋገረና እያሳመናቸው ሦስት ወር ሙሉ ምንም ሳይፈራ ፊት ለፊት ይናገር ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 19:8 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጳውሎስ ወደ ምኲራብ ሄዶ ለሦስት ወር ያኽል ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተከራከረና ሕዝቡን እያስረዳ በድፍረት ያስተምር ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 19:8 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ጳው​ሎ​ስም ወደ ምኵ​ራብ ገብቶ በግ​ልጥ አስ​ተ​ማረ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸ​ውና እያ​ሳ​መ​ና​ቸው ሦስት ወር ቈየ።

ሐዋርያት ሥራ 19:8 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ወደ ምኵራብም ገብቶ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተነጋገረና እያስረዳቸው ሦስት ወር ያህል በግልጥ ይናገር ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 19:8 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ወደ ምኵራብም ገብቶ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተነጋገረና እያስረዳቸው ሦስት ወር ያህል በግልጥ ይናገር ነበር።