ሐዋርያት ሥራ 18:26 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 18:26 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
እርሱም በምኵራብ በድፍረት ይናገር ጀመር፤ ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ፣ ወደ ቤታቸው ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ይበልጥ አስተካክለው አስረዱት።
ሐዋርያት ሥራ 18:26 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
እርሱ በድፍረት በምኲራብ መናገር ጀመረ፤ ነገር ግን ጵርስቅላና አቂላ በሰሙት ጊዜ ወደ ቤታቸው ወሰዱትና የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል አብራርተው ገለጡለት።
ሐዋርያት ሥራ 18:26 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
እርሱም በምኵራብ በግልጥ ይናገር ጀመር፤ ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ ወደ ማደሪያቸው ወስደው ፍጹም የእግዚአብሔርን መንገድ አስረዱት።
ሐዋርያት ሥራ 18:26 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
እርሱም በምኵራብ ገልጦ ይናገር ጀመር። ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜም ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት።
ሐዋርያት ሥራ 18:26 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
እርሱም በምኵራብ ገልጦ ይናገር ጀመር። ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜም ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት።