ሐዋርያት ሥራ 17:16 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 17:16 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ጳውሎስ በአቴና ሆኖ ሲጠብቃቸው ሳለ፣ ከተማዪቱ በጣዖት የተሞላች መሆኗን በማየት መንፈሱ ተበሳጨበት።
ሐዋርያት ሥራ 17:16 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ጳውሎስ በአቴና ሆኖ ሲላስንና ጢሞቴዎስን ሲጠብቅ ሳለ በከተማዋ ጣዖት መሙላቱን በተመለከተ ጊዜ በመንፈሱ ተበሳጨ።
ሐዋርያት ሥራ 17:16 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ጳውሎስም በአቴና ሆኖ ሲጠብቃቸው ከተማው ሁሉ ጣዖት ሲያመልኩ ባየ ጊዜ ልቡናው ተበሳጨ።
ሐዋርያት ሥራ 17:16 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ጳውሎስም በአቴና ሲጠብቃቸው ሳለ፥ በከተማው ጣዖት መሙላቱን እየተመለከተ መንፈሱ ተበሳጨበት።
ሐዋርያት ሥራ 17:16 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ጳውሎስም በአቴና ሲጠብቃቸው ሳለ፥ በከተማው ጣዖት መሙላቱን እየተመለከተ መንፈሱ ተበሳጨበት።