ሐዋርያት ሥራ 15:5 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 15:5 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ከፈሪሳውያን ወገን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው በመቆም፣ “አሕዛብ እንዲገረዙና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው” አሉ።
ሐዋርያት ሥራ 15:5 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ነገር ግን ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ አማኞች ተነሡና “አሕዛብ እንዲገረዙና የኦሪትን ሕግ እንዲጠብቁ ማድረግ ይገባል” አሉ።
ሐዋርያት ሥራ 15:5 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ነገር ግን ካመኑት ከፈሪሳውያን ወገን አንዳንዶች ተነሥተው፥ “ትገዝሩአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዝዙአቸው ዘንድ ይገባል” አሉ።
ሐዋርያት ሥራ 15:5 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ከፈሪሳውያን ወገን ግን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው፦ “ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል” አሉ።
ሐዋርያት ሥራ 15:5 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ከፈሪሳውያን ወገን ግን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው “ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል፤” አሉ።