Skip to content

ሐዋርያት ሥራ 15:22 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 15:22 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በዚህ ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከመላው ቤተ ክርስቲያን ጋራ ሆነው ከመካከላቸው አንዳንድ ሰዎችን መርጠው፣ ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋራ ወደ አንጾኪያ ለመላክ ወሰኑ፤ ከወንድሞችም መካከል ዋነኛ የነበሩትን በርስያን የተባለውን ይሁዳንና ሲላስን መረጡ፤

ሐዋርያት ሥራ 15:22 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከዚህ በኋላ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያን ሰዎች ሁሉ ጋር ሆነው ከጉባኤው መካከል ጥቂት ሰዎችን መርጠው ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ለመላክ ወሰኑ፤ ስለዚህ በወንድሞች መካከል በመሪነት መልካም ዝና የነበራቸውን በርሳባስ የተባለውን ይሁዳንና ሲላስን መረጡ።

ሐዋርያት ሥራ 15:22 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ከዚ​ህም በኋላ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሕዝ​ቡም ሁሉ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ አን​ጾ​ኪያ የሚ​ል​ኳ​ቸ​ውን ሰዎች ይመ​ርጡ ዘንድ ተስ​ማሙ፤ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸው መካ​ከ​ልም የተ​ማ​ሩ​ትን ሰዎች በር​ና​ባስ የተ​ባለ ይሁ​ዳ​ንና ሲላ​ስን መረጡ።

ሐዋርያት ሥራ 15:22 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ።

ሐዋርያት ሥራ 15:22 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ያንጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ።