ሐዋርያት ሥራ 14:8 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሐዋርያት ሥራ 14:8 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
በልስጥራንም፣ እግሩ ዐንካሳ የሆነና ከተወለደ ጀምሮ ፈጽሞ በእግሩ ሄዶ የማያውቅ ሽባ ሰው ተቀምጦ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 14:8 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
በልስጥራ እግሩ የሰለለ አንድ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው ከተወለደ ጀምሮ ሽባ ስለ ነበር በእግሩ ሄዶ አያውቅም፤
ሐዋርያት ሥራ 14:8 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
በልስጥራንም እግሩ የሰለለ፥ ከእናቱም ማኅፀን ጀምሮ ሽባ የሆነ፥ ከቶም ሂዶ የማያውቅ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 14:8 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
በልስጥራንም እግሩ የሰለለ፥ ከእናቱም ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ፥ ከቶም ሄዶ የማያውቅ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 14:8 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
በልስጥራንም እግሩ የሰለለ፥ ከእናቱም ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ፥ ከቶም ሄዶ የማያውቅ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር።