Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 10:41 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 10:41 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የታየውም ለሁሉ ሰው ሳይሆን፣ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ዐብረነው ለበላንና ለጠጣን፣ እግዚአብሔርም አስቀድሞ ለመረጠን ለእኛ ለምስክሮቹ ነው።

ሐዋርያት ሥራ 10:41 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የተገለጠውም አስቀድሞ በእግዚአብሔር ለተመረጡት ምስክሮች ነው እንጂ ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፤ እርሱ ከሞት ከተነሣ በኋላ እኛ ከእርሱ ጋር አብረን የበላንና የጠጣን ምስክሮቹ ነን፤

ሐዋርያት ሥራ 10:41 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ይኸ​ውም ለሕ​ዝቡ ሁሉ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን አስ​ቀ​ድሞ ለመ​ረ​ጣ​ቸ​ውና ምስ​ክ​ሮች ለሚ​ሆ​ኑት ብቻ ነው እንጂ፤ የመ​ረ​ጣ​ቸው የተ​ባ​ል​ንም እኛ ነን፤ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ ከተ​ነሣ በኋላ ከእ​ርሱ ጋር የበ​ላን የጠ​ጣ​ንም እኛ ነን።

ሐዋርያት ሥራ 10:41 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተመረጡ ምስክሮች ለሆንን ለእኛ ነው እንጂ፤ ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን።

ሐዋርያት ሥራ 10:41 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተመረጡ ምስክሮች ለሆንን ለእኛ ነው እንጂ፤ ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን።